በክልሉ በ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ከወሰዱ መደበኛ ተማሪዎች ውስጥ 44 በመቶው የማለፊያ ነጥብ አምጥተዋል- አቶ አንተነህ ፈቃዱ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ም/ ርዕሰ መስተዳድርየማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነ ፈቃዱ የ2016 የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።
አቶ አንተነህ በሰጡት መግለጫ በክልሉ 1መቶ 10ሺህ 772 ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና መውሰዳቸውን ተናግረዋል።
ከዚህም ውስጥ 48 ሺህ 728 ያህሉ 50 በመቶና በላይ የማለፊያ ያስመዘገቡ ሲሆን እነዚህም ከጠቅላላ ተማሪዎች ያላቸው ድርሻ 44 በመቶ መሆኑን ጠቁመዋል።
ከዚህም ውስጥ 24ሺህ 972 ወይም 42 በመቶ ያህሉ ሴቶች ናቸው ብለዋል።
በዓመቱ የተመዘገበው ውጤት ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ138% ዕድገት አሳይቷል ነው ያሉት ።
በዚህም መሠረት የማለፊያ ዝቅተኛ ነጥብ 50 በመቶ ሲሆን ለአካል ጉዳተኞች 45 በመቶ መሆኑን አስታውቀዋል።
በፈተናው ሙሉ ለሙሉ ተማሪዎችን ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች ብዛት 101 ሲሆን ከጠቅላላ ትምህርት ቤቶች ያላቸው ድርሻ 6 ነጥብ 7 በመቶ ነው።
ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ80 በመቶ ዕድገት እንዳለው ነው አቶ አንተነህ በሰጡት መግለጫ የገለጹት።
በዓመቱ ባለፉት ዓመታት አሽቆልቁሎ የነበረው የተማሪዎች ውጤት ለማሻሻል ቢሮው በርካታ ስራዎችን ማከናወኑን ያስታወሱት አቶ አንተነህ በዚህም መነሻ በዘንድሮ ዓመት በእጅጉ የሚበረታታ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል።
ለዚህም ስኬት መመዝገብ የክልሉ ርዕሰመስተዳድርና የመንግስት ዋና ተጠሪን ጨምሮ የትምህርት ሴክተር ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፣ የሆሳዕና ትምህርት ኮሌጅ መምህራና አመራሮች፣ አጠቃላይ፣ ተማሪዎች፣ ወላጅችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የነበራቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ያነሱት አቶ አንተነህ በራሳቸውና በክልሉ ትምህርት ቢሮ ስም ምስጋና አቅርበዋል።
ተማሪዎች በ https://ce.ministry.et/ ድረገጽ አድሚሽን ካርዳቸውን እያስገቡ ከዛሬ ጀምሮ ውጤታቸውን መመልከት እንደሚችሉ ተሙልክቷል።
በይዲድያ ተስፋሁን
Copyrights 2024. . All Rights Reserved.
Developed by NATNAEL ABATE